Showing posts with label የእማማ ጠቅላላ ማኀበር ልሣን. Show all posts
Showing posts with label የእማማ ጠቅላላ ማኀበር ልሣን. Show all posts

Saturday, September 15, 2018

የ34ኛ ዓመት የወንጌል አገልግሎት እነሆ

በሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር /ቤት መስከረም 6/2011/
34 ዓመት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተጀመረበትን ዓመት
ምክንያት በማድረግ የቀረበ አጭር ታሪክ
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው
ይህ መልእክት ለእስራኤል አንድ ጊዜ ተሰጥቶል የቆመ ብቻ ሳይሆን በየጊዜው ከሚነሳው ትውልድ ጋር ሲመላለስ የሚኖር የማያቋርጥ ትምህርት  ወንጌል ሲሆን በየጊዜው ተደጋግሞ ሊነገርም የሚገባው ነው፡፡
በእስራኤል መካከል በግ የሚያረባ ገበሬ ለበጎች ማደሪያ የሚሆን መግቢያውና መውጫው አንድ የሆነ ክብ ሆኖ በድንጋይ የታነጸ ጋጥ (በረት)ያበጁ ነበር፡፡ ፀሐይም መጥለቅ በሚጀመርበት ወቅት እረኛው ለምለም ሣር እያበላ ሲጠብቅ ከዋለበት መስክ የበጉን መንጋ ስብስቦ ወደ ማደሪያቸው ያስገባቸው ነበር፡፡
እረኛው ቀን እንደሚጠብቃቸው ሁሉ አውሬ እንዳይበላቸው ሌባ ሰርቆ እንዳይወስዳቸው ሌሊትም ቢሆን ራሱ ከመንጋው ማደሪያ በር ላይ ተገኝቶ ይጠብቃቸው ነበር፡፡
በትንቢተ ሕዝቅ. .3 16 እንደተባለው የእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌሃለሁ ስለዚህ አንተ ሐጢአተኛውን ሰው ከክፉ መንገድ እንዲመለስ ነግረህ ባታስጠነቅቅውና ባሐጢአቱ ቢሞት ደሙን ከእጅህ እፈልጋለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ከክፉ መንገዱ እንዲመለስ ነግረኸው ወይም አስተምረኸው ሳይመለስ ቢሞት አንተ ነፍስህን አድነሃልና በሕይወት ትኖራለህ ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት እግዚአብሔር ባሕታዊ /መስቀልን አስነስቶ ላከልን እኛም በቃሉ ተማረክን፡፡ 
     እንዲህ ያሉትንም የመንፈስ ረሃብተኞች ከቸሩ እረኛቸው ከክርስቶስ ጋር ልናስተዋውቃቸውና ከማዕድም ተመግበው  እንዲጠግቡ ልናደርጋቸው ታዘናል፡፡ የአውሬውም እራት እንዳይሆኑ ልንጠብቃቸው ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌም እረኛ በጎቹን የለመለመ ሣር እንዲነጩ የጠራ ውኃ እንዲጎነጩ ወደ መስክ የሚያሰማራቸው ከተኩላና ቀበሮ አፍ የሚጠብቃቸው ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለበጎቹ ጥቅምና ደኅንነት ጭምር የሚያስብ መሆን አለበት፡፡
      የመንጋው ጠባቂ የሆነው እውነተኛው እረኛችን ክርስቶስ ግን ስለበጎቹ ሕይወቱን ከመሰዋቱም  ሌላ የመንፈስ እረኃብተኞች ለሆነው ሁሉ ሕይወት መድኀኒት የሆነውን ቅዱስ ሥጋውን ዘወትር ይመግበናል፡፡ በመንፈስ ጥም ተይዘን ለምንሰቃየውም ክቡር ደሙን ጠጥተን እንድንረካ ሰጥቶናል ወደ እርሱም የምንመጣውን ወደ ውጭ አያወጣንም፡፡ሰለዚህ ነው ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ነውበለመለመ መስክ ያሳድረኛል ወደ እረፍትም ውኃ ይመራኛል ያለው፡፡

Monday, July 23, 2018

የዕማማ አመታዊ የጠቅላላ ጉባኤውን ስብሰባ አከናወነ

            በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ዛሬ ሀምሌ 15 ቀን 2010 ዓ.ም  የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር አመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀረበ ሲሆን እንደተለመደው ፕሮግራሙ በጸሎት ከተከፈተ ቡኃላ የሃይማኖት ዕውቀት ማስፋፊያ ማህበር መስራችና የበናይ ጠባቂ በሆኑት በሊቀ ትጉሃን መምህር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል የመክፈቻ ንግግር ከተደረገ ቡኃላ በቀትታ በእለቱ ሊከናወኑ ወደታቀዱት ፕሮግራሞች መላትመ
በአመቱ የተከናወኑ አጠቃላይ የስራ ክንውን ሪፖርት ማቅረብ
በውጭ ኦዲተር የተከናወነ የሂሳብ ምርመራ ሪፖርት በውጭ ኦዲተር ማቅረብ
ለ2011 ዓ.ም እቅድና በጀት ማቅረብና በጠቅላላ ጉባኤው ማጸደቅ
ላለፉት 5 ዓመታት ያገለገሉትን የቦርድ አባላት በክብር ማሰናበትና አዲስ ማስመረጥ ሲሆን

ፕሮግራሙ በታቀደለት ሰአት እንዲከናወን ለማድረግ ተችሎአል ፡፡ በወቅቱም የማህበሩ ስራአስኪያጅ እንደገለጹት በአመት ውስጥ ከ1.3 ሚሊየን ብር በላይ በማውጣት ዘርፈ ብዙ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በጥቂቱ ከ110 በላይ ሰባኪያንና ዘማሪያንን በመጠቀም በተላያዩ አህጉረ ስብከቶች ላይ ቃለ እግዚአብሄር እንዲሰበክ ተደርጎአል ፡ለበርካታ አቢያተ ቤተ ክርስቲያን ጧፍ እጣን ሻማ እንዲሁም ሙሉ አልባሳት ማደል ፡ ወጣቶችንና አባቶችን በመንፈሳዊ ኮሎጅ ማስተማርና ማስመረቅ የመሳሰሉት ይገኙበታል

Thursday, April 26, 2018

የማህበር ህጋዊ እውቅና ሰርተፍኬትና ሌሎች

የሃይማኖት እውቀት ማሰፋፊያ ማህበር እና የቤዛ ብዙሃን ምግባረ ሰናይ በጎ አድራጎት ማህበር ህጋዊ እውቅና ተሰጠን ለመሆኑ ይህንን መረጃ ማንበብና መረዳት ትችላላችሁ እንዲሁም የሊቀ/ትጉ/መ.ር ገ/መስቀል ኃ/መስቀል በኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተሰጣቸው ህጋዊ እውቅና በዚሁ መልእከት ውስጥ ሌሎችንም መረጃዎች የምታገኙ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን ፡፡
 
 
 

 


 

ክብረ ቅዱሳን 1


የዮሐንስ ወንጌል 2:1-12- John 2:1-12
በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ። የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው። ኢየሱስም። አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት። እናቱም ለአገልጋዮቹ። የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው። አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። ኢየሱስም። ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው። አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም። አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን


Monday, April 23, 2018

ስለ ማህበራችን አጭር መግለጫ

ስለ ማህበራችን አጭር መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይዎችና አራማጆች እንደምን አላችሁ እግዚአብሔር ይመስገን የሃይማኖት እውቀት ማስፋፍያ ማህበር ወይም በአጭሩ የእማማ ማህበር የዛሬ 33 ዓመት በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ውስጥ በሊቀ ትጉ ባሕታዊ /መስቀል /መስቀል መስከረም 12ቀን 1979 ተመሰረተ አላማው ወንጌል መስበክ ድሆችን መርዳት የገጠር ቤተ እና ገዳማትን ማገዝ ለሀገር ለወገን ምሕላ ጸሎት ማድረስ በንስሐ ቄደር እያስጠመቁ ሰዎችን ለንስሐ ማብቃት ዋና ዋና ተግባሩ ነው በመላው ዓለም የሚገኜው ማህበራችን በጎ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ምርጫ ይሰጣል እድሜ ልክ አባል ለመሆን አንድ ጊዜ 10 000ብር የክር አባል በየወሩ 100ብር ቁዋሚ አባል ለመሆን በየወሩ 5ብር በመክፈል